ወደዚህ ገጽ እንኳን ደህና መጡ!
-
የታረደው በግ
የክርስትያን ማዕከላዊ መልእክት ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁና የኃጢአት ይቅርታን እንዲያገኙ በተከፈለው ዋጋ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ የሚቻል የተደረገው በጌታ ኢየሱስ የመስቀል ሞት አማካኝነት ነው፡፡ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶ የመስዋዕትነት ለምን እንደነበረና “እርሱም የታረደው በግ” ተብሎ መጠራት ለምን እንዳስፈለገው ይች አጭር ጽሑፍ ታስረዳናለች፡፡ -
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ የሚባሉ ቅራኔዎች: የቅራኔዎች መኖር ውንጀላ
ብዙ ሙስሊሞች በተደጋጋሚ ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች ውስጥ ዋነኛው ያነጣጠረው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በእርሱ የሚቃረን መጽሐፍ ነው ይሉንና አንዳንድ የሚቃረኑ የሚመስሉ ጥቅሶችን ይጠቅሱልናል፡፡ ይህንን በተመለከተ በአራት ጸሐፊዎች የተዘጋጀው ጽሑፍ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ ስለሚባሉት 101 የእርስ በእርስ ቅራኔዎች አስገራሚ መልስን ይሰጣል፡፡ -
ዘመናዊ ሳይንስ በቁርአን ውስጥ ሊገኝ ይችላልን?
እንደ soc.religion.islam ዓይነት የዜና ቡድኖችና በሌሎችም አካባቢዎች በጣም ብዙ ጊዜ ልዩ የሆነ አንድ ነገር ብቅ ይላል፡፡ ይህም በቁርአን ገፆች ውስጥ ዘመናዊ ሳይንስ ይገኛል የሚል ማሳሰቢያን በተመለከተ ነው፡፡... ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ -
የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች
ይህ መጽሐፍ የመጀመሪያው ምዕራፍ መግቢያውና ሙስሊሞች በአጠቃላይ ቁርአን ከእግዚአብሔር መጣ የሚል እምነት እንዳላቸው የሚናገር ነው፡፡ ሙስሊሞች በሙሉ ያላቸው ይህ እምነትና መረዳት በሐቀኛ ምርመራ በመመሥረት የቁርአን ምንጭ ምንነት መገለጡ መከተል ያለባቸውን አሁኑኑ እንዲያስቡበት በጣም እንደሚረዳቸው ይታመናል፡፡
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ

