ደኅንነት በቁርአን

M. J. Fisher, M.Div.

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

መግቢያና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ንፅፅር

የዚህ ምዕራፍ ርዕስ አሳሳች ነው፡፡ ሙስሊሞች አልዳኑም፡፡ ይህንን እውነታ እያንዳንዱ ሙስሊም መቀበል አለበት ምክንያቱም በእስልምና ትምህርት ውስጥ ግልፅ የሆነ የደኅንነት ፅንሰ ሐሳብና ትምህርት የለም፡፡ ይህንንም የምንመለከተው ከዚህ ቀጥሎ ባሉት ሃያ ስምንት የቁርአን ጥቅሶች በሚያስረዱት መሠረት ነው፡፡ ደኅንነት ‹ወይንም እውነተኛ ንስሐ በመግባት በአዳኙ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የኃጢአትን ይቅርታ በመቀበል የዘላለምን ሕይወት እርግጠኝነት ማግኘት) ሙሉ በሙሉ የክርስትያን ልምምድ ነው ምክንያቱም ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው ‹እግዚአብሔር ከእኛ ጋር› የሆነው፡፡ በእሱም የሚያምኑትንና የተደገፉትን በትክክል እንደሚያድናቸው ያስተማረው እርሱ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ቁርአን ግን መሐመድን አዳኝ አድርጎ አላቀረበውም፡፡

አዳኝም ስለሌላቸው፣ ሙስሊሞች መታመን ያለባቸው በራሳቸው መልካም ስራ ላይ ብቻ ነው፣ ይህም ምናልባት በአላህ የምህረት ጊዜ ሽልማትን እንዲያገኙ ሊሆን ይችላል፡፡ ክርስትያኖች የሚያምኑት ግን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተሰቃየው በእነሱ ምትክ እንደሆነ ነው፣ ይህንንም እርሱ ያደረገው እነሱ የዘላለምን ሕይወት ‹የነፃ ስጦታ› ሆኖ እንዲቀበሉት ነው (ኤፌሶን 2.8-10)፡፡ ይህንንም ስጦታ በእምነት ተቀብለውታል ከዚያም በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀው ከዓለም አቀፏ ቤተክርስትያን ጋር አንድ ሆነዋል፡፡ ብዙ ሙስሊሞች እንደዚህ ዓይነቱ እምነት ለማህበረ ሰብ አደገኛ እንደሆነ ይሰማቸዋል፡፡ ምክንያቱም የሲዖል ቅጣት በማስፈራሪያነት ዘወትር መነገሩ መልካምን ስራና የፅድቅን ሕይወት ለመኖር የሚገፋፋ ነው በማለት ያምናሉና ነው፡፡ ደኅንነት የሚባለው ነገር ስጦታ ከሆነ፤ አንድ ሰው መልካምን ሕይወት ለመኖር ሊገፋፋው የሚችል ምንም ነገር አይኖርም በማለት ሙስሊሞች ያስባሉ፡፡

ይሁን እንጂ በየአገሩ ባሉት ብዙ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች የወላጅ አልባ ልጆች ማሳደጊያዎች እና ሌሎችም ቁጥር በሌላቸው መልካም መርሃ ግብሮች  ክርስትያኖች በዓለም ሁሉ ውስጥ እጅግ በጣም የታወቁ ናቸው፡፡ እነዚህ ጥሩ ስራዎች ሁሉ በክርስትያኖች የተሰሩት ወደ መንግስተ ሰማይ የመግቢያን መንገድ ለማግኘት ተብሎና ታስቦ ሳይሆን በክርስቶስ በኩል በመስቀል ላይ ስለተሰራላቸው የፀጋ ስራና የትንሳኤ ሕይወት እውቅናን ለመስጠት የተደረጉ ምላሾች ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር የክርስትያኖች በጎ አድራጎቶች ሁሉ በተደረገላቸው የእግዚአብሔር የነፃ የፀጋ ስጦታ መሠረት በመነሳሳት የተደረጉ በጎ ምላሾች ናቸው፡፡

አንድ ሙስሊም በዘላለማዊው የአትክልት ቦታ ውስጥ ለመግባቱ እርግጠኛነት እንዲሰማው ለማድረግ ቁርአን የሚሰጠው አንድ መንገድን ብቻ ነው፡፡ ይህም መንገድ የተመሰረተው በአንድ ሰው መልካም ስራ ላይ ብቻ ነው፡፡ የሚያስተምረውም አንድ ሰው ለእስልምና እምነት እየተዋጋ የሞተ ከሆነ በገነት ውስጥ የሚኖረውን ስጋዊ ደስታ ለመደሰት ይፈቀድለታል የሚል ነው፡፡

ስለዚህም ቁርአን  የሚከተለውን ይናገራል፡-

አዳኝ የለም፡- በፍርድ ቀን ማንም ሰው ማንንም ሰው ሊያድነው አይችልም (82.19፣ 35.18፣ 39.7)፡፡

ሥራዎች ይመዘገባሉ፡- እያንዳንዱ ሰው ጠባቂ አለው ስለዚህም የእያንዳንዱ ሰው መልካም ስራዎችና ክፉ ስራዎች ይመዘገባሉ፣ ስለዚህም በፍርድ ቀን ፃድቁ በደስታ ቦታ ሲቀመጥ ኃጢአተኛው ደግሞ በእሳት ውስጥ ይጣላል፣ እዚያም ምንም ደስታ የሌለበት ሲሆን ማምለጥም አይቻልም 82.10-15፡፡ በዚያን ቀን ጥቃቅን የሆኑት መልካም ነገሮችና መጥፎ ነገሮች ሁሉ ይገለጣሉ 99.7-8፡፡

ሚዛኖች፡- የእያንዳንዱ ሰው ስራ በሚዛን ይመዘናል፣ ይህም በፍርድ ቀን የሚመረመር ይሆናል፡፡ መልካም ስራዎቻቸው ከባዶች የሆኑላቸው እነሱ የዘላለም ደስታ ይኖራቸዋል፡፡ የእነሱም ስራዎቻቸው ቀላሎች ከሆኑ መኖሪያ ቤታቸው የሚሆነው በጥልቁ እሳት ውስጥ ነው 101.4-11፡፡

ሰይጣናት፡- አላህ በማያምኑት ላይ ሰይጣናትን ይልክባቸዋል ይህም የንዴት ዓመፅን በእነሱ ላይ ለማነሳሳት ነው 19.83፡፡

ፀሎቶች፡- እነዚያ የአላህን ዙፋን የያዙት እና ዙሪያውን የከበቡት ያለማቋረጥ የሚፀልዩት፣ ገነት መግባት የሚገባቸው ሙስሊሞች ይቅር እንዲባሉ ነው 40.7-9፡፡

ለሙስሊሞች ምህረት፡- አላህ ለፃድቃን ምህረትን ያደርጋል፡፡ ለእነዚያ ቸር ለሆኑትና በእሱ መገለጥ ለሚያምኑ፣ እነዚያ ነቢያትን የሚከተሉት (ማንበብንም መጻፍንም የማይችሉት)፣ በቶራህ (በብሉይ ኪዳን ሕግ) እና ወንጌል (አዲስ ኪዳን) ላይ  ስማቸው ተጠቅሶ የሚያገኙዋቸው ሰዎች 7.156-157፣ 39.9፡፡

የምስጢር መዋጮዎች፡- የምትሰጡትን ስጦታዎች ማሳወቅ ጥሩ ነው፣ ነገር ግን ለአንዳንድ ኃጢአቶቻችሁ ማስተሰርያ የሚሆነው ለድሃዎች በምስጢር ገንዘብን ከሰጣችሁ ነው 2.271፡፡

መልካም ስራዎች እጥፍ ይሆናሉ፡- የእያንዳንዱ ሰው ስራ በትክክል ይመዘናል ይህም እስከ ጥቃቅኗ ነገር ድረስ ነው፡፡ እያንዳንዱም መልካም ስራ እጥፍ ይከፈለዋል 4.40፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-

ከዚህ በላይ የቀረቡት ሃያ ስምንት የቁርአን ጥቅሶች በሙሉ የሚያሳዩት በእስልምና ውስጥ የደኅንነት እምነት አስተምህሮ እንደሌለ ነው፡፡ ሰዎች ገነት ውስጥ የሚገቡ ከሆነ፣ ቁርአን እንደሚያስተምረው ሊሆን የሚችለው በመልካም ስራዎቻቸው አማካኝነት የተነሳ ነው፡፡ ስለዚህም ከዚህ በላይ ባየናቸው በቁርአን ጥቅሶች መሠረት ግልፅ የሆነው እውነታ፣ አንድ የእስልምና እምነት ተከታይ ከእምነቱ የሚያገኘው የተረጋገጠ ዘላለማዊ ነገር የሌለው መሆኑን ነው፡፡ ታዲያ ሙስሊሞች ከእምነታቸው የሚጠቀሙት ዘላለማዊ ነገር ምንድነው?

የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ቅዱስና ፃድቅ ነው፡፡ እርሱ ኃጢአትን ይፀየፋል በኃጢአትም ላይ ፍፁም የሆነ ፍርድን ይፈርዳል፡፡ አንድ ኃጢአተኛ በእርሱ ቅዱስና ንፁህ ዓይኖች ፊት የሚያቀርበው ፍፁም የሆነና እግዚአብሔርን የሚያረካ ስራ ሊኖረው አይችልም፡፡ ይህ እውነታ ነው አዳኝ እንዲኖረን ያስገደደው፡፡ ስለዚህም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ ሆኖ ኃጢአተኞች  ሊቀበሉት የሚገባቸውን ፍርድ በራሱ ላይ ወስዶ በመሞት ደግሞም ከዚያ ሞት በድል በመነሳት እውነተኛ አዳኝ ሆነ፡፡

በኃጢአታቸው ከልብ ንስሐ ገብተው እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል እንዲቀበላቸው  ወደ እርሱ በመጡ ሰዎች ሕይወት ውስጥ ሁሉ አስደናቂ የሆነ መንፈሳዊ ለውጥ ተከናውኗል፡፡ የዘላለምም ሕይወትን ዋስትና አግኝተዋል፡፡ ይሄ እውነታ የሃይማኖተኝነት ጉዳይ አይደለም፣ ይህ የሕይወት ጉዳይ ነው በተለይም የዘላለም ሕይወት ጉዳይ ነው፡፡

ስለዚህም ለዚህ ገፅ አንባቢዎች የምናቀርበው ጥሪ እንደሚከተለው ነው፡፡ የኃጢአታችሁን ይቅርታ ለማግኘት ንስሐ ገብታችሁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር ይቅር እንዲላችሁ ብትጠይቁት ይቅርታንና የዘላለም ሕይወትን ዋስትና እንዲሁም እርግጠኝነትን ታገኛላችሁ፡፡ ወደ ብቸኛው አዳኝ ወደ ጌታ ኢየሱስ ኑ ምህረትንም ተቀበሉ እግዚአብሔር ይርዳችሁ አሜን፡፡

 

የትርጉም ምንጭ: Salvation,  Chapter 11 of "A Topical Study of the Qur'an From a Christian Perspective" by M.J Fisher, M.Div

ሙሉ መጽሐፉ በአማርኛ: ርእሳዊ የቁርአን ጥናት በክርስትና አይን ሲመረመር

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ