አጫጭር ዜናዎች

በሳውዲ አረቢያ የክርስቲያኖች ሰቆቃ ለምን ተዘነጋ?

የአለም አቀፍ የክርስትና ተቆርቋሬ (ICC) ድርጅት ሮብ April 11th, 2012 ጆን ሜንሆልድን ጠቅሶ እንዲህ ሲል አቅርቦታል፡

«በመሪነት አገራችን በአለም ነጻነትን ማስፋፋት ከፈለገች ወላዋይ አቋም መያዝ የለባትም። ከ2005 ጀምሮ መንግስታችን ሳውዲ አረቢያ ሃይማኖትን በተመለከት የምታደርሰውን የስብአዊ መብት ጥሰት አይቶ እንዳላየ ወደጉን አድርጎታል። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች የጸሎት ስብሰባ ስለአደረጉ ብቻ የሳውዲ መንግስት ለእስር መዳረጉ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚወገዝ ነው። ጥቁር ክርስቲያን ከሶስተኛው አለም የመጡ ቅጥር ሰራተኞች በሳውዲ ያለአግባብ መታሰርን አስመልክቶ የአለም የዜና አውታሮች እንደትልቅና እንደሚያጓጓ ዜና ባያወጡትም እንደ ዋና ዜና ሆኖ መቅረብ ነበረበት።»

ይህንን ስጽፍ በክርስትና እምነት ትንሳኤ ትልቅ አወደ ዓመት ሲሆን ክርስቲያኖች ስቅለትን ያከብሩታል። ሲኤንኤን(CNN) ደግሞ እዚህ ግባ የማይባል ዜና ስለ Kim Kardashian በትኖአል። የአሜሪካ መንግስት የአለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን(USCIRF) ያዘጋጀውን ብዙም የማይታወቀውን ሰነድ በአጋጣሚ በቅርብ በድህረ ገፅ ላይ አይቻለሁ። ለብዙ አመታት ካነበብኳቸው መካካል በ2012 አመታዊ ሪፓርት ውስጥ ያነበብኩት ሰነድ እጅግ ጠቃሚ ነው። USCIRF ተግባሩ ለፕሬዜዳንቱ፣ለአገር አስተዳደር ጸሐፊ እና ለፓርላማ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚደርሰውን የሃይማኖት ነፃነት ሰብአዊ መብት ገፈፋ በጽሑፍ ማቅረብ ነው። የእነሱም አስተያየት ይህን በሚያደርግ አግር አቋም መውሰድ ወይም እንዳላዩ ማለፍ ነበር። ለምንድነው በድረ ገፆች ላይ ያሉትን የምመረምረው? ታላቁ የሳውዲ ሼክ አብዱል አዚዝ ቢን አብዱላህ በቅርብ ጊዜ ተጠቅሶአል።

የክርስቲያን ሰቆቃ በሳውዲ አረቢያ ለምን ተዘነጋ? «በክልሉ (በአረብ ምደረ ሰላጤ) ያሉትን ሁሉን ቤተ ክርስቲያን መደምስስ አስፈላጊ ነው» የሚለው ዜና እጅግ አስደንጋጭ ነው ምክንያቱም የአረብ ምድረ ሰላጤ የሚያካትተው ሳውዲ አረቢያን፣ የተባበሩ አረብ ኤምሬቶችን፣ ካታርን፣ ክዌትን፣ ባህሬን፣ ኦማንና የመንን ነው። በተጨማሪም በሳውዲ አረቢያ ታላቁ ሙፍቲ በእስልምና ሃይማኖት ከፍተኛው  ስልጣን ነው። ዳሩግን በድህረ ገጽ ዜና ፍለጋ ላይ የዋሽንግተን ፖስትና ሁስትን ክሮኒክል ጭካኔ ያለበትን አባባሉን በማውገዝ በዋና ርእስነት አቅርበውታል። እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ የሩስያ፣ ኦስትሪያና የጀርመን ጳጳሳት የሳውዲ  ታላቁ ሙፍቲ ያለውን በመቃወም ያሰሙትን ጩሀት ሬውተር ብቻ ነበር እንደዜና ያቀረበው።

የካቶሊክ ጳጳሳት ኮንፈረንስ በኦስትሪያ የታላቁ ሙፍቲ ፋታዋ «የማይገባ» ስለሆነ ከሪያድ መንግስታዊ ማብራሪያ ጠይቋል። አባባሉ በአረብ አገሮች ብቻ ሳይሆን በአለም ዙሪያ ያሉትን ክርስቲያኖች አደጋ ላይ ይጥላል። እንደ USCIRF  ዘገባ «በሳውዲ አረቢያ በስልትና ቀጣይነት ያለው ከስርአት ውጭ የሆነ የሃይማኖት መብት ገፈፋ»አለ። ዘገባውም እንደሚለው መስከረም 11, 2001 አሜሪካ ላይ ጥቃት ከደረሰ 10 አመት በላይ ሆኖአል ነገር ግን የሳውዲ መንግስት ቃል የገባችውን  በተለይ የሃሳብን የህሊና ወይም የእምነት ነፃነት ለውጦች አላደረገችም። የሳውዲ መንግስት ቤተክርስቲያንን፣ ቤተመቅደሶችን እና ሌሎች ከእስልምና ጋር ያልተያያዙ የማምለኪያ ስፍራዎችን ከልክሎአል፤ በትምህርት ቤቶችና በድረ ገፆች የመማሪያ መጽሐፍት ላይ ለአመፅ የሚያነሳሱ ልዩነትን የሚያባብሱ መልእክቶችን ያስተላልፋል፤ አልፎ - አልፎ በግል በሚደረግ አምልኮ ጣልቃ ይገባል። በተጨመሪም ዘገባው እንደሚለው «መንግስቱ የውጭ አገር የሃይማኖት መሪዎች ሳውዲ አረቢያ እንዳይገቡ ቪዛ አሁንም እንደከለከለ ነው። በዚህም የተነሳ የተጎዱት የካቶሊክና የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ናቸው ምክንያቱም ካለካህን ቅዱስ ቁርባንን ማድረግ አይችሉምና። በግምት 800 ሺህ ክርስቲያኖች በሳውዲ ይገኛሉ። ብዙዎቹ በስራ ቪዛ የገቡ ካቶሊክ ፊሊፒኖች ናቸው። «35 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ታህሳስ 15, 2011 በግል አነሳሽነት የጸሎት ስብሰባ ተካፍላችኋል ተብለው ታስረዋል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ በምርመራ ጊዜ የአካል ጉዳት ደርሶብናል ብለዋል።» ሲል USCIRF በሪፖርቱ ላይ አስፍሮል።

በአለም አቀፍ የክርስትና ተቆርቋሬ (ICC) ድርጅት የሚመራ ተቃውሞ በማርች 26 ዋሽንግተን ዲሲ ሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ያለአግባብ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን እንዲፈቱ ለንጉስ አብዱላህ ጥያቄ አቅርቧል። የተካሄደው ዋሽንግተን ፖስት ቢሮ አጠገብ ቢሆንም ስለተቃውሞ ሰልፍ አንድም ዜና በድህረ ገፆች ላይ  አላየሁም። የኢትዮ-አሜሪካ የድህረ ገፅ መጋዚን ብቻ ስለተቃውሞ ጽፎአል። በመሪነት አገራችን በአለም ነፃነትን ማስፋፋት ከፈለገች ወላዋይ አቋም መያዝ የለባትም። መንግስታችን ሳውዲ አረቢያ ሃይማኖትን በተመለከተ የምታደርሰውን የስብአዊ መብት ጥሰት ከ2005 ጀምሮ አይቶ እንዳላየ ወደጉን አድርጎታል። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች የፀሎት ስብሰባ ስለአደረጉ ብቻ የሳውዲ መንግስት ለእስር መዳረጉ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚወገዝ ነው። ጥቁር ክርስቲያን ከሶስተኛው አለም የመጡ ቅጥር ሰራተኞች በሳውዲ ያለአግባብ መታሰርን አስመልክቶ የአለም የዜና አውታሮች እንደትልቅና እንደሚያጓጓ ዜና ባያወጡትም እንደ ዋና ዜና ሆኖ መቅረብ ነበረበት። የፓርላማ መሪዎቻችን የታሰሩት እንዲፈቱና የሳውዲው ሙፍቲን በአረብ ሰላጤ ያሉት ቤተክርስቲያኖች ይደምሰሱ ማለቱን ማውገዝ አለባቸው። የተባበሩት መንግስታት ሕገ መንግስቱንና መተዳደሪያ ደንቡን በሳውዲ አረቢያ የሃይማኖት ነፃነት መከበሩን እውን ማድረግ አለበት።
 
መሰረታዊ የሆነ የሰብአዊ መብትና የሃይማኖት ነፃነት ለውጥ በሳውዲ አረቢያ ካልተካሄደ አለማችን አሳሳቢ የደህንነት አደጋ ውስጥ ነው የምትገኘው። የሰው ልጅ መብት ተሟጋች ማርቲን ሉተር እንዳለው «ግፍ ባለበት ፍርድ በየትም ቦታ ይዛባል»፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

በብዙ ዜና ማሰራጫዎች ላይ የወጣውና እስከ አሁን ድረስ ምንም መፍትሔ ያላገኘው የ35 ክርስትያኖች በሳውዲ አረቢያ መታሰር አሳሳቢ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉ ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ውስጥ ሆነ በሌላ አገር እምነታቸውን በነፃነት እንዲከታተሉ መብት አላቸው፡፡ ስለዚህም መስጊድ መስራት ትምህርት ቤቶች መክፈት ይችላሉ፡፡ በሙስሊም አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ክርስትያኖች ግን እንደዚህ ያለ ነፃነት የላቸውም፡፡ እምነታቸውን በይፋ እንዲከታተሉ ፈቃድ ማግኘት ቀርቶ በድብቅም እንደማይፈቀድላቸው የሳውዲውና በሌሎችም አገሮች የሚከሰቱት ሁኔታዎች ግልፅ ናቸው፡፡

በሲሪያ ውስጣ አሁን ያለውን የሙስሊሞች የእርስ በእርስ ብጥብጥ አስታኮ ከ200 በላይ የሚሆኑ ሲሪያውያን ክርስትያኖች ታርደዋል፡፡ ሙስሊሞች እንደዚህ ዓይነት ግፍን በክርስትያኖች ላይ ስለምን ያደርጋሉ፣ የሙስሊም እምነት መሰረታዊ መርሆ በሰው ልጅ መብት፣ በሰው ልጅ መሰረታዊ ነፃነት እና ለሰው ልጅ ሕይወት ክቡርነት ምንም ግንዛቤ የለውም ማለት ነውን? ሙስሊሞች በተለያዩ የዓለም አገራት ውስጥ ሙስሊሞች በክርስትያኖች ላይ የሚፈፅሙት ግድያ፣ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እና የሚያሳዩት ጥላቻ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎች ለመጠየቅ ያነሳሳል፡፡

በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሲናገሩ እንሰማ የነበረው፤ ሙስሊሞች ለክርስትያን እምነት ትልቅ ዋጋ እንደሚሰጡና በሰውም መብት መከበር እንደሚያምኑ ነው፡፡ ታዲያ አሁን በሳውዲ ስቃይ ለሚያዩት ክርስትያኖች መፈታት ምን ያደረጉት ነገር አለ፡፡

ከዚህም በላይ በኢትዮጵያ የተለያየ ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩ እስልምናንም እንኳን የሚያስፋፉ፣ በተለያየ ስራ ላይ የተሰማሩና የሚኖሩ ሳውዲ አረቢያኖች እንዳሉ የዚህ ድረ ገፅ አዘጋጆች ያምናሉ፡፡ እነርሱስ በአገራቸው ውስጥ በኢትዮጵያውያን ክርስትያኖች ላይ ስለሚፈፀመው ግፍ ምን ያሉት ነገር አላቸው?

እነዚህን ጥያቄዎች ሙስሊም አንባቢዎች እንዲያስቡባቸው ያክል ብናቀርብም፤ ሙስሊሞች እንዲገነዘቡ የምንፈልገው የክርስትያኖች አምላክ ሕያው የሆነው እግዚአብሔር በንፁሃን ክርስትያኖች ላይ ስለሚደርሰው ግፍ ፍርዱን እንደሚሰጥ እንዲገነዘቡ ሲሆን፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ለእራሳቸው የእምነታቸውን ምንነት እንዲረዱም ጭምር ነው፡፡

እስልምና ከሰማይና ምድር ፈጣሪ እግዚአብሔር የመጣ ከሆነ ስለምን ለሰዎች መብት እና ነፃነት አይቆምም፤ ስለምንስ የሌላውን እምነት ተከታዮች ይጠላል፣ ስለምንስ የሌላውን እምነት ተከታዮች ያሳድዳል? የሰዎች ሁሉ ሕይወት ምንጭ የሆነው እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠውን ሕይወት የሰብዓዊ መብት እና ሰላም ስለምን ከሰዎች ላይ ይወስዳሉ፡፡ የሙስሊም እምነት ይህን በማድረጉ የሰዎችን ፈጣሪ እግዚአብሔርን በሌላ መንገድ መቃወሙ አይደለምን?

እውነተኛው እስር ቤት!

የክርስትያኖች አምላክ እግዚአብሔር ለእውነተኛ ክርስትያኖች ያደረገላቸው ነገር ከአዕምሮ በላይ ነው፡፡ ክርስትያኖችን መታሰርና መሰደድ ከዚህ ድንቅ እምነት ለቀንጣት ታክል አይመስላቸውም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ክርስትያኖች በሙሉ ከኃጢአት እስራት ነፃ የወጡና የተፈቱ ለዘላለም ክብር የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ስለዚህም በእውነተኛው መንፈሳዊ እስራት ውስጥ ያሉ ሰዎች በስጋና በጊዜያዊ እስራት ውስጥ ቢያስገቧቸው በጣም አይደነቁም፡፡ የሳውድ አረቢያው ንጉስና ባለስልጣኖቹ ሁሉና የእምነቱ አስተማሪዎች በሙሉ በመንፈሳዊው እስራት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ጽሑፍ የምታነቡና ከክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለምን ሕይወት ያላገኛችሁ ሁሉ በተመሳሳይ እስራት ውስጥ ትገኛላችሁ፡፡ ይህንን እውነት ታውቃላችሁን?

ለታሰሩ አሳሪዎች - የንስሐ ጥሪ!

የዚህ ገፅ አዘጋጆች ትልቅ ናፍቆትና ፀሎት የሃይማኖት መለወጥ እና አለመለወጥ ጉዳይ አይደለም፡፡ አንባቢዎች ያላችሁበትን የነፍሳችሁን ሁኔታ በትክክል እንድትረዱና ከነፍሳችሁ እስራት ነፃ መውጣት የምትችሉበትን መንገድ እንድታዩ ነው፡፡ ሁሉን ከሚያውቀው እግዚአብሔር ዘንድ በፀጋው ምህረትን ያልተቀበሉ ሁሉ በኃጢአት እስራት ውስጥ ነው ያሉት፡፡ ከዚህ እስራት የሚያወጣ ሃብት ሃይማኖት ስልጣኔና እውቀት የለም፡፡ እግዚአብሔር ግን ከኃጢአት እስራት ውስጥ መውጫ መንገድን በክትስቶስ በኩል አዘጋጅቷል፡፡ ይህንንም መንገድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል 14.6 ውስጥ እንዲህ በማለት ገልጦታል፡ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” እርሱ ነው የዘላለም ሕይወት መንገድ በእርሱ የታመኑ ብቻ ናቸው ከነፍሳቸው እውነተኛ እስራት ውስጥ በእርሱ ምህረትና ኃይል ነፃ በመውጣት አዲስን ሕይወት ሊያገኙ የሚችሉት፡፡

አንባቢዎች እናንተም ከታሰራችሁበት የኃጢአት እስራት ነፃ ስለመውጣት ማሰብ አለባችሁ፣ ይህንን የምታገኙት በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም ወደ ጌታ ኢየሱስ እንድትመጡ ንስሐም በፊቱ እንድትገቡ እና ምህረቱን በመቀበል ነፃ እንድትሆኑ እንጠይቃችኋለን እግዚአብሔር በምህረቱ ይርዳችሁ አሜን፡፡

የትርጉም ምንጭ:  "Why is Christian persecution in Saudi Arabia ignored?" (ICC) or "Why is Christian persecution in Saudi Arabia ignored?"

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ