አጫጭር ዜናዎች 

በኢራን ውስጥ በክርስትያኖች ላይ የሚደርሰው የግፍ ጥቃት አላቆመም
በJamie Dean, WORLD News Service
Monday, November 04, 2014
ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

ህዳር 4 ቀን በስደት ውስጥ ላሉት ቤተክርስትያናት በሚደረገው ዓለም አቀፍ የፀሎት ቀን የኢራናዊው ፓስተር ቤናም ኢራኒ ስለ ክርስትያን እምነቱ በእስር ላይ በመሆን 900 ቀናትን አስቆጥሯል፡፡ በአገር ደህንነት ላይ ወንጀል ፈፅመሃል በመባል በፓስተሩ ላይ የተፈረደበት ፍርድ አራት ገና ዓመታት ይቀረዋል፡፡ እነዚያ ወንጀሎች የሚያጠቃልሉት ክርስትያን አግልግሎትን መስጠትንና ለሙስሊሞች ስለ ወንጌል መናገርን ነው፡፡

የ42 ዓመቱ ኢራኒ በተፈረደበት ፍርድ ከሁለት ዓመት በላይ እስር ቤት ውስጥ ታስሯል ከፍተኛ የሆነም የጤና ማሽቆልቆልን አይቷል፡፡ ክርስትያናዊው ቡድን Present Truth Ministries እንደዘገበው የዚህ ያገባና የሁለት ልጆች አባት ከኢራናዊ ጥበቃ ሰራተኞች ድብደባ የተነሳ አንዳንዴ እንዳይንቀሳቀስ ከሚያደርገው የአንጀት በሽታ ይሰቃያል፡፡ የእስር ቤቱ አዛዦችም ብቁ የሆነን ሕክምና አያቀርቡም፡፡

በመስከረም ወር የኢራኒ ጠበቃ ለእስር ፍርዱ ይግባኝ አቅርቦ ነበር፡፡ ይህንንም ያደረገው የኢራን ባለስልጣኖች ለ11 የሕሊና እስረኞች ምህረትን ባደረጉበት ጊዜ ነበር፤ ዳኛው የእርሱንም ጉዳይ እንዲመለከትለት ፓስተሩ ተስፋ አድርጎ ነበር፡፡ Present Truth Ministries ሪፖርት ያደረገው ነገር ዳኛው ኢራኒን ለመፍታት የሚችልበት አንዱ መንገድ እንደሚከተለው እንደሆነ ነው “ንስሐ ገብቶ ወደ እስልምና ከተመለሰ ነው”፣ የድርጅቱ ሪፖርት ቀጥሎም እንዳቀረበው “እርሱ ይህንን ወደ እስልምና የመመለስን ሁኔታ አይቀበልም እናም እስር ቤት ውስጥ ይቆያል” ነበር ያለው፡፡

ብዙ ክርስትያኖች በኢራን እስር ቤት ውስጥ ቀርተዋል፡፡ ከዜሮ ነጥብ አምስት በመቶ በታች ክርስትያኖች ባሉበት አገር ውስጥ ለክርስትና እምነት መሰጠት አሁንም አደገኛ ነው፡፡ አንድ ወንድ ወደ ክርስትና ከተለወጠ ቅጣቱ ሞት ነው፡፡

ይሁን እንጂ ቢያንስ አንድ ክርስትያን ወንድ ባለፈው ዓመት ከሞት አምልጧል፡፡ ፍርድ ቤቱ አንድ ኢራናዊንና ዮሴፍ ላካርዳኒ የተባለውን ፓስተር ፈትቶ ለቆታል ይህም ባለፈው ዓመት በእርሱ የሞት ፍርድ ላይ ዓለም አቀፉ ማህበረ ሰብ ከዳር እስከዳር ጩኸቱን ካሰማ በኋላ ነው፡፡  ላካርዳኒን ፍርድ ቤቱ ከሶት የነበረው እስልምናን የከዳ በማለት ነበር፡፡

ሌሎቹ ሁኔታዎች ቀላል ፍርድ ነው የሚያስከትሉ ናቸው፣ ነገር ግን በጣም መጠነ ሰፊ የሆነ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡ በትውልድ ኢራናዊው አሜሪካዊው ፓስተር ሰኢድ አብዲኒ በቴህራን ኢቪን እስር ቤት ውስጥ ነው ያለው እርሱም ክርስትያናዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፉ የ 8 ዓመት እስርን እየታሰረ ነው፡፤

የእርሱ ሚስት ናግሜህ በመስከረም ወር በኒውዮርክ ከተማ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ባለቤቷ እንዲለቀቅ የሚጠይቅ አቤቱታዋን ለአዲሱ ኢራን ፕሬዜዳንት ለሃሰን ሮአሂኒ ሰዎች በእጅ እንዲሰጡላት አድርጋለች፡፡ ነገር ግን በሲ.ኤን.ኤን በተደረገ ቃለ መጠይቅ አዲሱ ፕሬዜዳንት የተናገረው ነገር በኢራን የሕግ ሂደት ውስጥ ጣልቃ ለመግባት እንደማይችል ነው፡፡

በኢራን ውስጥ ለተያዙት ክርስትያኖች ጥፋተኞች ናቸው የሚባሉት በጣም በፍጥነትና ምንም ጠቃሚ ባልሆኑ ማስረጃዎች ነው፣ ብዙዎችም ያንን ሂደት ለኢራናዊ ፍርድ ቤቶች አንገብጋቢ ስጋት እንዳልሆነ ሆኖ አግኝተውታል፡፡ በሐምሌ ወር ብቻ አንድ ዳኛ ስምንት ኢራናዊ ክርስትያኖችን እስከ ስድስት ዓመት በሚደርስ ፍርድ በእስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩ ፈርዶባቸዋል ይህም “በአገር ውስጥ ደህንነት ላይ ጥፋት አድርሰዋል” በሚልና እንዲሁም “በአገሪቱ ስርዓት ላይ የተቃውሞ ፕሮፓጋንዳ አስፋፍታችኋል” በሚል ክስ ነው፡፡ ባለ ስልጣኖቹ ክርስትያኖችን በምሽት ፀሎት አገልግሎት ላይ አስረዋቸዋል፤ ነገር ግን ክርስትያኖቹ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳላደረጉ ገልፀዋል፡፡

ምንም ዓይነት ዓለም አቀፍ ትኩረት ያልተሰጣቸው ሌሎች ብዙ ክርስትያኖች ብዙ ዘመናት በእስር ቤት ውስጥ ያሳልፋሉ፡፡ ኢራናዊው ፓስተር ፋርሺድ ፋትሂ በክርስትና አገልግሎቱ ምክንያት ሦስት ዓመታት ያህል በእስር ቤት ውስጥ አሳልፏል፡፡ የ34 ዓመቱን ፋትሂን ዳኛው የፈረደበት በኢቪን እስር ቤት ውስጥ ለስድስት ዓመት እንዲታሰር ነው፡፡

የዚያን ፍርድ የአንድ ዓመት እስር ፋትሂ ያሳለፈው በብቻ እስር ነው፣ በዚያም እያለ መርማሪዎች እንዴት ስሜት ጎጂ ነገሮችን በመጠቀም ፈቃዱን ለመስበር ይሞክሩ እንደነበር  ከእስር ቤት በጻፈው ደብዳቤ ገልጧል (እርሱም ባለስልጣኖቹ በውሸት ሚስቱ እንደተያዘችና አባቱም በልብ ድካም በሽታ እንደተሰቃየ ይነግሩት እንደነበር አብራርቷል)፡፡

ፋትሂ የሰጠው መግለጫ ግን የእርሱ እምነት ጠንክሮ እንደቀጠለ ጭምር ነው፡፡ በጥቅምት መጀመሪያ ላይ Voice of the Martyrs የተባለ የክርስትያን ድርጅት ፋትሂ የጻፈውን ሌላ ደብዳቤ በሪፖርታቸው ላይ አትሞታል፡፡ እርሱም ያለው “በዓለም ዙሪያ ሁሉ የሚገኙ በክርስቶስ ወንድሞቼና እህቶቼ ለእምነታቸው ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ እያሉ እኔ እንዴት አጉረመርማለሁ? በቅርብ ጊዜ በፓኪስታን በቤተክርስትያን ፊት ለፊት የተሰበሰቡ ክርስትያኖች እንደተገደሉ ሰምቻለሁ፡፡ እንዲሁም አንዲት ወጣት ሴት ልጅ ስለ ወንጌል እንዴት ወላጆቿን እንዳጣች ሰምቻለሁ ሆኖም ግን አሁንም እርሷ ወንጌልን (የምስራቹን ዜና) ለሌሎች ለማካፈል ፈቃደኛ ናት፡፡ ስለዚህም እኔ እነዚህን ሁሉ የወንጌል ጀግናዎች ስመለከት እኔ ስለማየው ስቃይ እንዴት አድርጌ ላማርር እችላለሁኝ”? በማለት ተናግሯል፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ

በኢራን ውስጥ የሚገኙ ክርስትያኖች የሚሰቃዩትን ስቃይ በጣም በጨረፍታ የሚያሳየው ዜና በአዕምሯችን ውስጥ ብዙ ነገሮችን እንድናወጣና እንድናወርድ ያደርገናል፡፡ ቀጥሎም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመጠየቅ ይገፋፋናል፡፡ የእስላም አገሮች ጥቂት የሆኑትን የአገራቸውን ክርስትያኖች ለምን ይጠሏቸዋል? ለምንስ ያሳድዷቸዋል? ሰላማዊና በቁጥር አናሳ የሆኑት ክርስትያኖች በእርግጥ ለእስልምና መንግስታት ስጋቶች ናቸውን?

እስልምና የሰላም እምነት ከሆነ ለሌሎች ሰዎች እና ለተከታዮቹ ሰላምን በተግባር የማያሳየው ለምንድነው? እንበልና አገራችን በእስላም አገዛዝ ውስጥ ብትወድቅ፣ በኢራን በግብፅ እና በሌሎች አገሮች ክርስትያኖች ላይ የሚሆነው ተመሳሳይ ነገር በእኛ አገር የማይሆንበት ምን ምክንያት ይኖራል?

ይሁን እንጂ እኛ የሰው ልጆች በምድር ላይ የምንኖረው ለተወሰኑ ዓመታት ብቻ ነው፡፡ አንድ ቀን ሁላችንም ከዚህ ዓለም ተለይተን በእውነተኛው አምላክ ፍርድ ፊት እንቀርባለን፡፡ የእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል እንደሚል በክርስቶስ ያመኑ የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉ ለዘላለምም ከጌታቸው ጋር ይኖራሉ፡፡ ለክርስቶስ የታሰሩ በግፍ የተሰቃዩና በግፍም የተገደሉ እንዲሁም በእውነቱ ላይ በመቆም እራሳቸውን ለመገደልም የሰጡት ሁሉ ከክርስቶስ ጋር በመንግስቱ ለዘላለም ይኖራሉ፡፡

በእስራት በግፍ በመሰቃየት ሲሰደዱ ክርስትያኖች በእምነታቸው ፀንተው የሚቆሙት ለዚህም አቋም ብርታት የሆናቸው ምስጢሩ ምንድነው? መልስ የሚሆነው በክርስቶስ በኩል የመጣውን የዘላለም መንግስት ስጦታ በእምነት መቀበላቸው ነው፡፡ የእውነተኛው የእግዚአብሔርን ምህረት በነፃ ማግኘታቸውና የመንግስተ ሰማይ ወራሽነታቸው እርግጠኝነት ስላላቸው ነው፡፡ በእርግጠኝነትም የሕይወትን ምስጢርና ዓላማ ከእግዚአብሔር ስለተቀበሉና ይህንንም እውነት በምንም ምድራዊ ነገር ከመለወጥ መሰቃየትንና መሞት በመምረጣቸው ነው፡፡

አንባቢዎች ሆይ የሕይወት ዓላማና ምስጢር ገብቷችኋልን፡፡ የምትኖሩት ለምንድነው? ስትሞቱ የምትሄዱት ወዴት ነው? ለእነዚህ ጥልቅ ጥያቄዎች መልስን የምታገኙት ከየት ነው? የዚህ ገፅ አዘጋጆች እነዚህን ነገሮች እንድታውቁ መጽሐፍ ቅዱስን እንድታነቡና ወደ ወንጌል አማኝ ቤተክርስትያን በመሄድ የምስራቹን ዜና እንድትሰሙ ይጋብዟችኋል፣ እግዚአብሔርም በምህረቱ ይርዳችሁ፡፡


Reference (የመረጃ ምንጭ): http://www.worldmag.com/2013/10/iran_s_crackdown_on_christians_not_letting_up

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ