ሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና

ክፍል አስር- የሴቶች መንፈሳዊ አቋም

[ክፍል አንድ] [ክፍል ሁለት] [ክፍል ሦስት] [ክፍል አራትና አምስት] [ክፍል ስድስት] [ክፍል ሰባትና ስምንት] [ክፍል ዘጠኝ]

M. Rafiqul-Haqq and P. Newton

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

 

ጥሩ ሚስትን ሐዲት የሚገልጣት እንደሚከተለው ነው፡ ‹ጥሩ ሚስት፣ ባሏ ሲጠይቃት፣ ትታዘዘዋለች፣ እርሷን ሲመለከት እርሱን ታስደስተዋለች፣ መሐላን ቢያስምላት ትፈፅምለታለች እርሱም ከእርሷ ቢርቅ እራሷንና ንብረቱን ሁሉ ትጠብቅለታለች› Mishkat al-Masabih, Book 1, duty towards children Hadith No. 43. (ኢብን ማጋህ)፡፡ ‹በጣም ጥሩ ሴቶች እጅግ በጣም ውብ የሆነ ፊት ያላቸውና ጥሎሻቸውም እርካሽ የሆኑት ናቸው› Ihya' 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, vol. II, Kitab Adab al-Nikah, p. 45፡፡ ‹ጥሩ ሚስት ከዚህ ዓለም ውጭ ናት ምክንያቱም በሚመጣው ዓለም ላይ እንድታተኩር ነፃ እንድትሆን ትረዳሃለችና፡፡ ይህንንም የምታደርገው የቤት ስራዎቿን በማከናወን ነው (ባሏ እንዲሰራ ከማድረግ ይልቅ) እንዲሁም ባሏን በግብረ ስጋ ግንኙነት እንዲረካ በማድረግ እርሱን ከግብረ ስጋ ግንኙነት ፈተና በመጠበቅ ነው› Ihya' 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, vol. II, Kitab Adab al-Nikah, p. 35፡፡

ሴቶች የወንድን የዘላለም መድረሻ ሊወስኑ ይችላሉ ይህም የዝሙት ኃጢአትን እንዳይፈፅሙ በመጠበቅ ነው፣ ይሁን እንጂ ሴቶች እራሳቸው የሚታዩት ለወንዶች በጣም አደገኞች ሆነው ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ ጋዛሊ የሚቀጥለውን ሐዲት ዘግቧል፡ ‹ሴት በምትመጣበት ጊዜ የምትመጣው ልክ እንደሰይጣን ሆና ነው› Ihya' 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, vol. II, Kitab Adab al-Nikah, p. 33. Also quoted in Sahih Muslim, English translation, Hadith No. 3240፡፡ እንዲሁም የሚታመነው ከእነርሱ ብዙዎቹ የሚገቡት በሲዖል ውስጥ እንደሆነ ነው፡፡

‹ነቢዩ አለ፡ ‹ከእኔ በኋላ ምንም ሌላ ጥፋትን አልተውኩኝም ከወንዶች ይልቅ እጅግ ክፉ የሆነ ጥፋት ለሴቶች ነው› Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. vii , Hadith No. 33 (ቡካሪ ተቀባይነት ያለው ሐዲት)፡፡

ዶክተር ኤም አል-ቡቲ ለሙስሊም ልጃገረዶች ንግግር ሲያደርግ እንዲህ አለ፡ ‹ወንድን የሚያሰቃየው ይህ መከራ በእናንተ ምክንያት እንደሆነ እወቁ› Dr. Mohammad Sa'id Ramadan al-Buti, Ela kul Fataten Tu'min be-Allah, Mu'asasat ar_Risalah, Beirut, 1987, Eighth edition, p. 19፡፡ ቁርአን 3.13 በመተንተን (ወንዶች በደህና የለበሱት ነገር፡ ሴቶችን፣ ልጆችን፣ ወርቅንና ብርን መቆልል፣ የፈረሶች ምልክቶች ከብቶችና እርሻ የመመኘትን ፍቅር ነው)፡፡ ዶክተር ቡቲ ያለው፡ ‹እግዚአብሔር ሴትን የሚመለከታት በሰዎች መንገድ ላይ ባስቀመጠው እንደ መጀመሪያ ደረጃ ምኞቶች ነው ... ስለዚህም ሴት በወንድ ሕይወት ውስጥ እጅግ በጣም ታላቅ ስቃይ ናት› Dr. Mohammad Sa'id Ramadan al-Buti, Ela kul Fataten Tu'min be-Allah, Mu'asasat ar_Risalah, Beirut, 1987, Eighth edition, p. 16፡፡

‹የአላህ ነቢይ ለሴት ልጁ ለፋጢማ እንዲህ አላት፡ ‹ለሴት በጣም ጥሩ የሆነው ምንድነው? እሷም መለሰች፡ ‹ወንድን አለመመልከቷና በወንድም አለመታየቷ ነው› እሱም በእሷ፤ በመልሷ በመደሰት አቀፋትና እንዲህ፡ ‹የተፈጠረበትን የመሰለ ዘር› አለ፡፡ የመሐመድ ተከታዮች መስኮቶችንና በግድግዳዎቻቸው ላይ ያሉትን ቀዳዳዎች ይከልሉ ነበር፤ ስለዚህም ሴቶቻቸው ወንዶችን እንዳይመለከቱ ... ... ‹ኦማርም እንዲህ አለ ‹ሴቶችን በጥሩ ሁኔታ አታልብሷቸው ከዚያም በቤት ውስጥ ይቀራሉ› ምክንያቱም በተቦጫጨቀ ልብስ ወደ ውጭ አይወጡምና፡፡ እንዲሁም እርሱ እንዲህ አለ፡ ‹አይሆንም የሚለውን ቃል የምትናገረውን ሴታችሁን አግኟት› Ihya' 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, vol. II, Kitab Adab al-Nikah, p. 53፡፡

ቡካሪ የሚከተለውን ሐዲት መዝግቧል፡ ‹ኦ ሴቶች! ምፅዋትን ስጡ እንደምመለከተው ከሆነ በሲዖል እሳት ውስጥ ከሚኖሩት ነዋሪዎች ብዙዎቹ እናንተ ሴቶች ናችሁ› Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. 1, section 'A menstruating woman should not fast', Hadith No. 301፡፡ እንዲሁም ሙስሊም የመዘገበው፡ ‹በገነት ውስጥ ካሉት ነዋሪዎች መካከል ሴቶች በጣም ጥቂቶቹ ናቸው› Sahih Muslim, English translation, Kitab Al-Riqaq, chapter MCXL Hadith No. 6600፡፡

ዶክተር መሐመድ አል-ቡቲ ዘመናዊው ጸሐፊ አብዛኛዎቹ ሴቶች ሲዖል ውስጥ የሚገቡበት ምክንያት አድርጎ የተመለከተው ነገር እነሱ በጣም ጠቃሚ በሆነው ስራዎቻቸው ላይ ስለ ወደቁ ነው ስለዚህም ወንዶችን እንዲወድቁ አድርገዋል› Dr. Mohammad Sa'id Ramadan al-Buti, Ela kul Fataten Tu'min be-Allah, Mu'asasat ar_Risalah, Beirut, 1987, Eighth edition, p. 21፡፡ ስለዚህም ሴቶች የሚወክሉት ለወንዶች አምልኮ እና የዘላለም መድረሻቸውን በመወሰን በኩል ታላቁን የማሰናከያ ግድግዳ (ግርዶሽ) ሆነው ነው ይህም የሚከተለው ሐዲት እንድጻፈው ነው፡ ‹ሴቶች ባይኖሩ ኖሮ እግዚአብሔር በእውነት በእውነት ይመለክ ነበረ› Kanz-el-'Ummal, Vol. 21, Hadith No. 825፡፡ ‹በአገሬ (በሕዝቤ) ውስጥ ምንም የሆነ መቅሰፍት አይኖርም ከሴቶችና ከአልክሆል ሌላ› Kanz-el-'Ummal, Vol. 21, Hadith No. 829፡፡ ‹ሴቶችን በታዘዙበት ዕለት ወንዶች ጠፍተዋል› Kanz-el-'Ummal, Vol. 21, Hadith No. 831፡፡

መደምደሚያ፡

ከእስልምና እምነት ውስጥ የመጡ ሴቶች በእንደዚህ ዓይነት እምነት ላይ ቢያምፁ ምንም ሊያስደንቀን አይገባም፡፡ አንዲት እንዲህ ዓይነት ሴት ዶ/ር ሳዳዊ እንደጻፈው፡

‹የጋብቻ ተቋም ለሴቶች ከሚለው ይልቅ ለወንዶች በጣም የተለየ ሆኖ ነው የቀረበው፣ እንዲሁም ለባሎች የተሰጠው መብት ለሴቶች ከተሰጡት በጣም የተለየ ነው፡፡ በእርግጥ ‹የሴቶች መብት› የሚለውን ቃል መጠቀም ምናልባትም ትክክለኛ ላይሆን ይችላል፣ ምክንያቱም በእስላሞች የጋብቻ ስርዓት ውስጥ (ሥር) ሴት ምንም ሰብዓዊ መብት የሚባል የላትምና፣ ይህም ባሪያ በባሪያ ስርዓት ውስጥ መብት አላት ብለን ካላሰብን በስተቀር፡፡ ጋብቻ ሴቶችን በተመለከተ የሆነው ባርነት ለባሪያዎች እንደሆነው ነው ወይንም ለሠራተኞች ስራን መስራት ሰንሰለታዊ ግንኙነት እንደሆነው ነው› Nawal El Sa'dawi, The Hidden Face of Eve, Zed Press, London, 1980, pp. 139, 140፡፡

በዚህ አባባሉ ዶ/ር ናዋል ሳዳዊ የሙስሊም ዓመፀኛና ሊበራል ፈላስፋ ከሆነ፣ ተመሳሳዩን አቋም ከጻፈው ከታላቁ የሙስሊም ምሁርና ፈላስፋ ከጋዛሊ ደግሞ የሚከተለውን እንስማው፣ ከሰባት ዓመታት ገደማ በፊት እርሱ ሁኔታውን ሲያጠቃልለው እንደሚከተለው ነው የተናገረው፡ ‹በጉዳዩ ላይ በጣም የሚያረካውና የመጨረሻው ቃል የሚሆነው ጋብቻ የባርነት ዓይነት መሆኑ ነው፡፡ ሴትየዋ የወንዱ ባሪያ ናት ስለዚህም የእርሷ ስራ ለባሏ ፍፁም ታዛዥነት ነው እርሱ ከእሷ ስብዕና በሚያዝዘው ነገር ሁሉ፡፡ መሐመድ እንዳለው፡ ‹አንዲት ሴት በሞቷ ጊዜ የባሏን ሙሉ ማረጋገጫ ያገኘች ከሆነ የእራሷን ቦታ የምታገኘው በገነት ውስጥ ነው› Ihya' 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, vol. II, Kitab Adab al-Nikah, p. 64፡፡

ኢህያ ዑለም ኢድ-ዲን ጋዛሊ ይህንን አረፍተ ነገር ያሰፈረበት ጽሑፍ በብዙ ምሁራን ዘንድ እጅግ በጣም የተመሰገነ ነው፡፡ በጣም ታዋቂው ኢማም ናዋዊ ስለ እርሱ እንዲህ ብሏል፡ ‹ኢህያ ያቀረበው ልክ እንደ ቁርአን ሆኖ ነው› Ihya' 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, vol. II, Kitab Adab al-Nikah, p. 6፡፡ ሚስት የወንድ ባሪያ ናት የሚለው እምነት እንደ ራዚ ባሉት ታላላቅ ምሁራንም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነው፡፡ Razi, commenting on the Qur'an 33:51፡፡ እንዲሁም ኢን አል-አራባይ ከዚህ በፊት በጥሎሽ ክፍያ ላይ (የተናገረውን) እንዳየነው ነው› Ibn al-'Arabi, Ahkam al-Qur'an, part one, p. 63፡፡

ሴቶች የወንዶች ባሪያዎች ናቸው የሚለውን በመቀበል በኩል ዘመናዊ ጸሐፊዎች እንደ ጋዛሊ ግልፅ አይደሉም፡፡ ነገር ግን ሴቶች ከወንዶች ዝቅ ያሉ መሆናቸውን ተቀብለዋል፡፡

አንድ ዘመናዊ ጸሐፊ የተናገረው እንደሚከተለው ነው፡ ‹ለልብሷ፤ ለፋሺን፣ ለፀጉሯ የምታስብን አንዲት ሴትና፤ የልጆችን ሃላፊነት በሴቶች ፈንታ ወስዶ የእርሷን ዕድለ ቢስነትና ችግር ስለ እርሷና ለልጆቹ ሲል ሃላፊነት ከወሰደው ሰው ጋር እርሷን ማነፃፀር ሎጂካዊም ትክክልም ያልሆነ ነገር ነው› Tuffaha, Ahmad Zaky, Al-Mar'ah wal-Islam, first edition, Dar al-Kitab al-Lubnani, Beirut, 1985, pp. 33፡፡

ከዚያም ቆየት ብሎ የሚከተለውን ጨምሯል፡ ‹በእስላምና፤ በሕግ ሴት ከወንድ ጋር እኩል ናት ... ነገር ግን ሴት በማህበራዊ ዋጋዋና በተጨባጭ መብቶች አንፃር ከወንድ ጋር እኩል አይደለችም፣ ምክንያቱም የሚያዝና ታዛዥ፣ ታላቅና ታናሽ፤ አዋቂና ደንቆሮ፤ ዕብድና ጤነኛ፤ ፃድቅና ኃጢአተኛ፤ ትጉና ሰነፍ፤ ብርቱና ደካማ እንዴት እኩል ሊሆኑ ይችላሉ? ስለዚህም እኛ በሕግ ፊት የሚኖርን እኩልነትና በሰዎች ማህበራዊ ዋጋ ፊት ያለውን እኩልነት (በፍፁም) ማደባለቅ የለብንም› Tuffaha, Ahmad Zaky, Al-Mar'ah wal-Islam, first edition, Dar al-Kitab al-Lubnani, Beirut, 1985, pp. 37፡፡

አንዲት ሴት ከዚህ በላይ ባለው መሠረት ያልተገለጠ ዝቅተኛ ማህበራዊ ግምት ቢኖራት፤ ጋዛሊ፤ የእስላም ‹ዓለት› ተብሎ የሚጠራው (ሁጋት አል-ኢስላም) ያ ዝቅተኛ ማህበራዊ ግምት ምን እንደሆነ አጥርቶታል፣ እንዲሁም በእራሱ እውነተኛ ስም ጠርቶታል ያም ‹ባሪያ› በማለት ነው፡፡ ይሁን እንጂ መሐመድ፤ ወንድን ከሴት ጋር ሲያነፃፀር የሴትን ትክክለኛ ዋጋ ሰጥቷል፤ ይህም እንደሚከተለው በተናገረ ጊዜ ነበር፤ ‹አንድን ሰው በሌላ ሰው ፊት እንዲሰግድ ያዘዝኩኝ ቢሆን ኖሮ አዝዝ የነበረው ሚስቶችን በባሎቻቸው ፊት እንዲሰግዱ ነበር ...›፡፡ ይሁን እንጂ ይህ የመሐመድ አባባል የባሪያና የጌታ ዓይነት ግንኙነት አይደለም ነገር ግን በፈጣሪና በፍጡር መካከል ወዳለው ግንኙነት ከፍ ብሏል እንጂ፡፡

እዚህ ነጥብ ላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነገር ሁሉም ሙስሊም ከዚህ በላይ ያለውን ትምህርት እንደማይከተለው ነው፡፡ ይህንን በተመለከተም የሚከተሉት ሐዲቶች በጣም አብራሪዎች ናቸው፡ ‹በኢብን ዑማር የተነገረው፡ ነቢዩ በሕይወት ይኖር በነበረ ጊዜ እኛ ከሚስቶቻችን ጋር በነፃነት የመጫወትንና የመዝናናትን ጊዜ እንርቅ ነበር፣ አለበለዚያ ስለ እኛ አንድ መለኮታዊ መገለጥ ይመጣ ነበር፡፡ ነገር ግን ነቢዩ ከሞተ በኋላ ግን እኛ ከሚስቶቻችን ጋር በነፃነት መጫወትንና (ማውራትን) መዝናናትንም ጀመርን፡፡ Sahih Bukhari, English translation by M. Muhsin Khan, Vol. VII, Hadith No. 115፡፡

በኡርዋ የተተረከው፡ ነቢዩ አቡ በከርን ጠየቀው አይሻን ያገባ ዘንድ፡፡ አቡ በከርም አለ፡ ‹ነገር ግን እኔ ያንተ ወንድም ነኝ›፡፡ ነቢዩም አለ፣ ‹በአላህ ሃይማኖትና በእርሱ መጽሐፍ አንተ የእኔ ወንድም ነህ፣ እርሷ ግን (አይሻ) ለእኔ እንዳገባት የተፈቀደች ናት› Sahih Bukhari, English translation by M. Muhsin Khan, Vol. VII, Hadith No. 18፡፡ (መሐመድ ሃምሳ ዓመት ሲሆነው አይሻ ግን ስድስት ወይንም ሰባት ዓመት ነበረች በዚያን ጊዜ፣ ነገር ግን ጋብቻው እርሷ የፀናው እርሷ ዘጠኝ ዓመት ሲሆናት ነው)፡፡

ነጥቡ ይህ ነው፤ ጠንካራ የሃይማኖት መሪ ባለበት ቦታ ብዙው ሕዝብ ይማረክና አስተምህሮውን ይከተላል፡፡ አስተምህሮውን በጣም በቅናት የሚያምነውና የሚያስተምረው የአስተምህሮውንም ተግባራዊ መሆን የሚጠይቀው አመራሩ ነው፡፡ በምዕራቡም ዓለም እንኳን አንዳንድ የሙስሊም መሪዎች፣ ለእነዚህ አስተምህሮዎች ተግባራዊነትን ይጠይቃሉ፡፡ ለምሳሌም ያህል በአውስትራሊያ ውስጥ የሙስሊም ምሁር የሚከተለውን አስተያየት ሰጥቷል፡ ‹የብዙ ጋብቻ (ፖሊጋሚ) ሕጋዊ መሆን አለበት በጋብቻ ውስጥ አስገድዶ መድፈር ወንጀል መሆኑ መጥፋት አለበት  ብሏል፤ ... እሱም የተከራከረው ሴት ባሏን አስገድዶኛል በማለት መክሰስ የለባትም በማለት ነው› The Sun-Herald, an Australian news paper, April 28, 1991, p. 21፡፡

እነዚህን ትምህርቶች፤ ሙስሊሞች ሁሉ ባይከተሏቸውም እንኳን ትምህርቶቹ ግን እዚያ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህም እነዚህን ትምህርቶች የማይከተልና አሁን ለስሙ ብቻ ሙስሊም የሆነ ሰው በጣም ትጉ አማኝ ወደመሆን ሊመለስ ይችላል፡፡ እርሱም እነዚህን ነገሮች አድራጊ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም እንዲያደርጉ ያስገድዳል፡፡ (ይጣራል ወይንም ያስተምራል)፡፡ 'Not Without My Daughter'  በተባለው ፊልም ውስጥ ኢራናዊው ሰው ለትንሽ ሴት ልጁ ያረጋገጠላት በአንድ ወቅት እንደ አሜሪካውያን እንደ የፍራፍሬ ሳምቡሳ እንደነበረ ነገር ግን አሁን ልክ እንደ ሆሚኒ ጥብቅ ሙስሊም ለመሆን ሊቀየር እንደሚችል ነው፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው እውነታ የአንዳንድ ሰዎች የግል አስተያየት አይደለም፣ ነገር ግን በቁርአንና በሐዲቶች ላይ ያለውን የአላህን ፈቃድ የሚወክል ነገር ነው፡፡ ቁርአን በጥቁርና ነጭ የሚያስተምረውን ሐዲት ደግሞ በቀለማት ያስተምረዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የተጠቀሱት ሐዲቶች ከእስላም መንፈስና ከቁርአን ትምህርት ጋር በሚገባ አብረው የሚሄዱ ናቸው፡፡ ሐዲት እንደዚያ ባይሆን ኖሮ፣ በቀጥታ በሰዎች የተቀናበረ ነው ተብሎ ገና እስልምና ከጀመረበት ዘመን ጀምሮ ገና ያኔ ከአስራ ሦስት መቶ ዓመታት በፊት ወዲያ ይጣል ነበር እንጂ አሁን አይደለም፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ሐዲቶች የተቀናበሩት በሙስሊሞች መካከል በጊዜያቸው እጅግ በጣም አጥባቂ በነበሩት ሰዎች ነበር፣ እንዲሁም ከአንድ ሺ ዓመታት በላይ በእስላማዊ ጽሑፎች ውስጥ እንደ እናት ጽሑፎች ሲጠቀሱና ከዓመት ዓመት ሲታተሙ ነው ያሉት፡፡ በቁራን እይታ ከዚህ በላይ ያለው ሐዲት አልተነቀፈም አልተወገደምም፡፡ ጥያቄን የፈጠረው አሁን በሌላ ብርሃን ሲገለጥ ነው፡፡

ከዚህ በላይ የቀረቡት ጥቅሶች የተለያዩና፣ አፈንጋጭ ወይንም ያልተለመዱ ምሳሌዎች አይደሉም ነገር ግን በእስልምና ውስጥ ሴቶችን በተመለከተ ስላለው አመለካከት ወጥ የሆኑ የዋና ዋናዎቹን አመለካከት የሚወክሉና ተቀባይነት ያላቸው  ናቸው፡፡

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ እኛ የራሳችንን አስተያየት በጣም ዝቅ አድርግን ነው የጠበቅነው ይህም አንባቢ በእኛ አተረጓጎም ከልክ በላይ እንዳይወሰድ ነገር ግን የራሱ የሆነ መደምደሚያ ላይ እንዲመጣ ነው፡፡

እኛ ማየት የምንችለው ቁርአን፣ የሐዲት ድምፅ፣ የቁርአን ተንታኞች፣ የሙስሊም ሊቃውንት፣ ጥንታዊዎቹም ሆኑ ዘመናዊዎቹ ወንዶች በሴቶች ላይ ስላላቸው የበላይነት አስተምህሮ ወጥ የሆነ አመለካከት እንዳላቸው ነው፡፡ ይሁን እንጂ በእስልምና ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል ናቸው በማለት የሚናገሩ ደግሞ አሉ፡፡ የዚህን ዓይነት ንግግር ከሚያቀርቡት መካከል አንዳንዶቹ ከዚህ በላይ ስላሉት ጽሑፎች ምንም እውቀት የሌላቸው ናቸው፣ ይህም ልክ "Mohammad, a messenger of God". በሚለው ፊልም ውስጥ እንዳለው ጉዳይ ነው፡፡ የፊልሙ ጽሑፍ የተዘጋጀው በሙስሊም ምሁራን ነው፣ እነሱም በዚህ ጽሑፍ ላይ ያሉትን የመነሻ ጽሑፎችን እንዲሁም ከዚያም በላይ በሚገባ ያውቃሉ፡፡

ይህ ጽሑፍ የማይታመን ነው ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ፣ ከዚህ በላይ የቀረቡትን ማገናዘቢያዎች በሙሉ ለእራሳችሁ ተመልከቱ፣ ይህንን ተከታታይ ጽሑፍ በችኮላ አንብባችሁት ከሆነ ደግሞ እባካችሁ ደግማችሁ አንብቡት እና የራሳችሁን መደምደሚያ ውሰዱ፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

ከዚህ በላይ በተደጋጋሚ እንዳየነው ሴቶችን በተመለከተ በንፁህ እስላም ዘንድ የሚገኘው አመለካከት አሁንም እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ለምሳሌ ‹ሴት ሰይጣን ናት›፣ ‹ሴት ለወንድ እጅግ በጣም ታላቅ ስቃይ ናት›፤ ‹ሴቶች ባይኖሩ ኖሮ እግዚአብሔር በእውነት፣ በእውነት ይመለክ ነበረ›፣ ‹ሴቶች የወንዶች ባሪያዎች ናቸው› የሚሉትን በዚህ ክፍል ላይ ብቻ አይተናል፡፡ በራሱ በመሐመድም አንደበት የተነገረውንና ወንድ እንደ አምላክ ሴት እንደ ዝቅተኛ ፍጡር የመወሰዷን ፍንጭ ሁሉ ተገንዝበናል፡፡

እውነትን ለሚፈልጉ ሰዎች አሁንም፣ አሁንም የሚነሳው ጥያቄ ሙስሊሞች በሴቶች ላይ ያላቸው ይህ እምነትና አስተምህሮ ምንጩ ማነው? የሰማይና የምድሩ ፈጣሪ እግዚአብሔር ወይንስ በእሱ ስም የተቀናበረ የሰዎች ባህልና ልማድ ነው? የጥያቄዎቹ መልሶች በምድር ስላለው ሕይወታችን እና ከሞት በኋላም ስለሚጠብቀን ፍርድና ሕይወት ትክክለኛ አመለካከት እንዲኖረን የሚመራን ነው፡፡

አንባቢዎች ሆይ!! የጥያቄዎቹን መልሶች በትኩረት፣ የምር እንድታስቡበትና ከዚህ በፊት በአዘጋጆቹ ለቀረቡት ጥሪዎች መልስ ለመስጠት እንድትዘጋጁ አሁንም በእግዚአብሔር ፍቅር ጥሪን እናቀርብላችኋለን፡፡

እውነተኛው አምላክ ጌታ እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡ አሜን፡፡

 

የትርጉም ምንጭ:  The Place of Women in Pure Islam  

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ